Wednesday, August 31, 2011

Waters recede across East, but storm victims suffer

MILLBURN, New Jersey (Reuters) - Floodwaters finally started to recede from areas of the northeast devastated by Hurricane Irene but many communities were still underwater on Wednesday and relief workers battled cut-off roads and raging rivers to deliver emergency supplies.

Saturday, August 13, 2011

እንኳን ለጾመ ፍልሰታ በሰለም አደረሳችሁ፤

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን፡፡

 ኢትዮጵያ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የአሥራት አገር ናት፡፡ ሊቃውንትም ነቢያት የተነበዩትን ትንቢት የቆጠሩትን  ሱባዔ መሠረት በማድረግ ቅድስት ድንግል ማርያም በኪደተ እግሯ ኢትዮጵያን መባረኳን ያስተምራሉ፡፡ «ነቢዩ ዕንባቆምየኢትዮጵያ ድኳኖች ሲጨነቁ ዐየሁ፤» ዕንባ. 3፡7 ብሎ የተናገረው ቃለ ትንቢት እመቤታችን የኢትዮጵያን አውራጃዎች ለመባረኳ ማስረጃ መሆኑን ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ይተረጉማሉ፤ ያመሠጥራሉ፡፡

Thursday, August 4, 2011

እግዚአብሔር፡እረኛዬ፡ነው፥

     መዝሙር፡22፡(23)።
የዳዊት፡መዝሙር።
1፤እግዚአብሔር፡እረኛዬ፡ነው፥የሚያሳጣኝም፡የለም።
2፤በለመለመ፡መስክ፡ያሳድረኛል፤በዕረፍት፡ውሃ፡ዘንድ፡ይመራኛል።
3፤ነፍሴን፡መለሳት፥ስለ፡ስሙም፡በጽድቅ፡መንገድ፡መራኝ።
4፤በሞት፡ጥላ፡መካከል፡እንኳ፡ብኼድ፡አንተ፡ከእኔ፡ጋራ፡ነኽና፥ክፉን፡አልፈራም፤በትርኽና፡ምርኵዝኽ፡እነር ሱ፡ያጸናኑኛል።
5፤በፊቴ፡ገበታን፡አዘጋጀኽልኝ፡በጠላቶቼ፡ፊት፡ለፊት፡ራሴን፡በዘይት፡ቀባኽ፥ጽዋዬም፡የተረፈ፡ነው።
6፤ቸርነትኽና፡ምሕረትኽ፡በሕይወቴ፡ዘመን፡ዅሉ፡ይከተሉኛል፥በእግዚአብሔርም፡ቤት፡ለዘለዓለም፡እኖራለኹ።



The Lord is my shepherd; I shall not want.  He maketh me to lie down in green pastures: he leadeth me beside the still waters.  He restoreth my soul: he leadeth me in the paths of righteousness for his name's sake.  Yea, though I walk through the valley of the shadow of death, I will fear no evil: for thou art with me; thy rod and thy staff they comfort me.  Thou preparest a table before me in the presence of mine enemies: thou anointest my head with oil; my cup runneth over.  Surely goodness and mercy shall follow me all the days of my life: and I will dwell in the house of the Lord for ever.

Wednesday, August 3, 2011

የሥነ ልቡና አገልግሎት ለወጣቶች

የሥነ ልቡና አገልግሎት ለወጣቶች

የአሸናፊነት ምስጢር”

በዶ/ር የማነ ገ/ማርያም

 ሰዎች እንደ ተፈጥሮአዊ ጠባያቸውና ዝንባሌአቸው መሠረት በአራት ቦታ ልንመድባቸው እንደምንችል የየሀገሩ የሥነ አእምሮ ወይም የሥነ ልቡና ጠበብት ያረጋግጡልናል፡፡

Tuesday, August 2, 2011

ትምህርተ ጋብቻ

ትምህርተ ጋብቻ ክፍል ፦ ፩

« መጋባት በሁሉ ዘንድ ክቡር ነው፤» ዕብ ፲፫፥፬

          ጋብቻን ባርኮና ቀድሶ ለሰው ልጅ የሰጠው እግዚአብሔር ነው። በመሆኑም ጋብቻ የእግዚአብሔር ጸጋ ነው። ስለዚህ በዓይን ምኞት ተጋርደው፥ በሥጋ ፍላጐት ተነድተው ፥ በስሜት ፈረስ ጋልበው ፥ የሚገቡበት ሳይሆን ፦ በጸሎት እና በምልጃ ፈቃደ እግዚአብሔርን ጠይቀው የሚፈጽሙት ታላቅ ምሥጢር ነው።

ቅድስት አርሴማ

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን::


እናታችን ቅድስት አርሴማ እግዚአብሔርን በቅንነት ያገለግሉ ከነበሩ  ካህናት ወገን ከሆኑ ከቅዱስ ቴዎድሮስና ከእናቷ ቅድስት አትናሲያ በስዕለት ተወለደች፡፡
ሰማዕቷ ቅድስት አርሴማ ብሉይን ሐዲስን ተምራ እያነበበች እንዲሁም በተግባር እየተረጎመች ዘወትርም በጸሎት ትተጋ እንደነበር ገድሏ ይተርካል፡፡ በዚህ ዘመን ድርጣድስ የሚባል በአርመን የነገሠ አረማዊ ንጉሥ ለጣዖት የሚሰግድ' ፀሐይንም የሚያመልክ' ክርስቲያኖችንም እኔ ለማመልከው አምላክ መስገድ አለባችሁ በማለት መከራ ያጸናባቸው ነበር፡፡

Friday, July 29, 2011

ክርስቲያናዊ ሥነ - ምግባር


በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን ::
ክርስቲያናዊ ሥነ - ምግባር
‹‹ መልካሙን ሥራችሁን አይተው በሰማያት ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ ብርሃናችሁ እንዲሁ በሰው ፊት ይብራ›› ማቴ. 5፡16

የመንፈሳዊ ትምህርት ማሰሪያው የምስጢራት መወሰኛው/የመጀመሪያው/ በጥሩ ሥነ ምግባር እራስንና ሌሎችን ቀርጾ መገኘት መሆኑን እምነታችንንና ምግባራችንን በጥሩ ሥራ መግለጽ አለብን ያዕ.2፡14
አንድ ሰው ጥሩ ወይም መጥፎ ሥነ ምግባር አለው ስንል ሥነ ምግባሩን በሁለት ነገሮች ማየት አለብን፡፡
1.  ውጫዊ ሥነ ምግባር
2.  ውስጣዊ ሥነ ምግባር
ነፍስና ስጋ እንደማይለያይ ሁሉ ሃይማኖትና ምግባር አይለያዩም፡፡ ያዕ. 2፡14

የሥነ ምግባር ሕግጋት

ሕግ ማለት ለማድረግ የሚያዝ ከማድረግ የሚከለክል ውሳኔና ሥርዓት ነው፡፡ ማንኛውም ክርስቲያን በእግዚአብሔር ዘንድ ቅድስናን አግኝቶ ይኖር ዘንድ የሥነ ምግባር ሕጎች የትኞቹ እንደሆኑ ግብራቸውና ስልታቸውን ለይቶ ማወቅ ይኖርበታል፡፡

       የሥነ ምግባር ሕጎች


*መንፈሳዊ / አምላካዊ/ ሕግ             *ሥጋዊ /አለማዊ/ ሕግ


* ኢ - ጽሑፋዊ ሕግ          *ጽሑፋዊ ሕግ        * የቤተክህነት ሕግ         * የቤተመንግስት ሕግ


*ሕገ ልቡና           * ሕገ ሕሊና               *ብሉይ ኪዳን         *ሐዲስ ኪዳን
                  
         (አስርቱ ትዕዛዛት)           (ስድስቱ ቃላተ ወንጌል)

- ክርስቲያን ሁሉ መንፈሳዊነትም ሥጋዊነትም ያለው ምድራዊ ፍጡር እንደመሆኑ እርሱንም የሚመለከተው ሕግ ሁለት ጠባይ ወይም በሁለት ክፍል ያለው ሕግ ይሆናል፡፡ ይኸውም
            - መንፈሳዊ/አምላካዊ/ ሕግ
            - ሥጋዊ ሕግ በመባል የሚታወቅ ነው፡፡

መንፈሳዊ /አምላካዊ/ ሕግ ለሰው ሁሉ ከልዑል እግዚአብሔር በተፈጥሮና በጽሑፍ የተሰጠው ሲሆን ዘለዓለማዊ በመሆኑ እና ከእግዚአብሔር በመገኘቱ መንፈሳዊ ሕግ ተብሏል፡፡

ኢ - ጽሑፋዊ ሕግ በሁለት ይከፈላል፡፡
-    ሕገ ልቡና
-    ሕገ ሕሊና

- ሕገ ልቡና፡- ይህ ሕግ በሰው ልቦና አንድ ጊዜ ከተጻፈ በኋላ ሳያረጅ ሳያፈጅ ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲተላለፍ ያለ የኖረ የተፈጥሮ ሕግ ነበር፡፡ ሮሜ. 1፡14 ሕገ ልቡና የተባለው ሰው በተባለው ሁሉ በልቦናው ተጽፎ የሚገኝ እያንዳንዱ ሰው ማንም ሳያስተምረው ክፉውንና ደጉን ለይቶ ሳይነግሩት እንዲያውቅ የሚያደርገው ስለሆነ ነው፡፡

 ሕገ ልቦና ሕገ ተፈጥሮአዊ ወይም ሕገ ጠባያዊ እየተባለ የሚጠራ ሲሆን ሰው የሚመሰገነው በተፈጥሮ የተሰጠውን ይህንን ሕግ በንጽሕና በመያዙና በማዳበሩ ነው፡፡
የሰው ልጅ ክፉውን ለይቶ ያውቅበት ዘንድ የተሰጠው ሕግ ነው፡፡

ሕገ ሕሊና፡- ሕገ ሕሊና ወይም ሕሊናዊ ሕግ የእግዚአብሔር ድምጽ ለነፍስ የሚተላለፍበት በማናቸውም ክርስቲያን ሁሉ አድሮ የሚሠራ ሥነ ምግባራዊ ሕግን እንድንፈጽም የሚያነቃ አርፈን እንቀመጣለን ብንል እረፍት የሚነሳ ነው፡፡ አንድ ሰው ነፍስ አጥፍቶ እንደሆነ የሚከስ አልምቶም ከሆነ እንዲደሰት የሚያደርግ የሕሊና ዳኛ ነው፡፡

- ይኽ ሕግ አንድ ግብር እንዲፈጸም ወይም እንዳይፈጸም ማስጠንቀቂያና ምርጫን የሚያደርግ ሲሆን ከተደረግ በኋላ መጥፎ እንደሆነ መጸጸትን ሐዘንን ያመጣል መልካም ከሆነ ደግሞ ደስታን መጽናናትን ይሰጠናል፡፡ ማንኛውም የክርስትና ተከታይ የሆነ በስሙ የተጠራ ግን ሁሉ ፍለጋውን የሚከተሉ ሁሉ የራሱን ሕሊና ምርጫ ማክበር የእግዚአብሔርን ድምጽ መስማት ግዴታው ይሆናል፡፡ እየተጠራጠረ እያመነታም የሚሠራ ሰው ሁሉ ከሕሊናው ግምት ውጭ ይሠራል ማለት ነው፡፡ ይህም እርሱን መበደል ነው፡፡ ሮሜ. 14፡23 ስለዚህ ሳይሠራ ያመልጣል ከሁሉ አስቀድሞ በምንሠራው ሥራ እንደ ሃይማኖታችን ጽናት መጠራጠር አይገባንም፡፡ ይህንን ሁሉ ለማስወገድ ከሁሉ በፊት

1.  ጸሎት መጸለይ ማለት የሚሠሩትን ሁሉ ‹‹ ወይኩን ፈቃድከ ›› ብሎ መጠየቅ
2.  ዓለማዊ ማንኛውም ከእግዚአብሔር ፍቅር የተነሳ የእሱን አምልኮትና ፍቅር መግለጫ መሆን ይኖርበታል፡፡ አምላክ ሰውን አፍቅሮ አንድያ ልጁን ለእኛ አሳልፎ ቤዛ እንደሰጠ ሁሉ ዮሐ. 3፡16
3.  ስለ እግዚአብሔር ክብር ተብሎ የሚሰራ መሆን ይኖርበታል 1ቆሮ 10፡31
4.  ስለ ባልንጀራው ፍቅር መሆን ይገባዋል፡፡

አሥርቱ ትዕዛዛት

      ከእግዚአብሔር አምላክ በቀጥታ በሙሴ አማካኝነት ለእስራኤላውያን የተሰጠ ሕግ ነው፡፡ የተሰጡትም እስራኤላውያን ከግብጽ ከወጡ በ3ኛው ወር ፋሲካን ካከበሩ በ3ኛው ቀን በደብረ ሲና ሰፍረው ሳለ ነበር፡፡ ዘፀ. 19፡1-4 በዘዳ. 34፡28 ዘዳ. 4፡13 ላይ አሥሩ ትዕዛዛት አሥር መሆናቸውን እንረዳለን፡፡
በዝርዝር ተጽፈው የሚገኙት ግን በዘዳ. 20፡ 3 እና17 እና ዘዳ. 5፡5-21 ላይ ነው፡፡ አሥርቱ ቃላትና ስድስቱ ቃላተ ወንጌል ለእስራኤል ዘስጋና ለእስራኤል ዘነፍስ የተዘጋጁ ስለሆነ ሁላችንንም ይመለከታል፡፡ እነርሱም፡-

1.  ‹‹ እግዚአብሔር አምላክህ እኔ ነኝ፡፡ ከእኔ በቀር ሌሎች አማልክት አይሁኑልህ የማናቸውንም ምሳሌ የተቀረጸውን ምስል ለአንተ አታድርግ፤ አትስገድላቸው፤ አታምልካቸው ›› ዘፀ. 20፡2-6
2.  ‹‹ የእግዚአብሔር የአምላክን ስም በከንቱ አትጥራ፡፡ ›› ዘፀ. 20፡7
3.  ‹‹ የሰንበትን ቀን ትቀድሰው ዘንድ አስብ /አክብረውም/ ›› ዘፀ. 20፡ 8
4.  ‹‹ አባትህንና እናትህን አክብር ›› ዘዳ. 20፡12
5.  ‹‹ አትግደል ›› ዘፀ. 20፡13
6.  ‹‹ አታመንዝር ›› ዘፀ. 20፡14
7.  ‹‹ አትስረቅ ›› ዘፀ. 20፡15
8.  ‹‹ በሐሰት አትመስክር ›› ዘፀ. 20፡16
9.  ‹‹ አትመኝ ›› ዘፀ. 20፡17
10.  ‹‹ ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ ›› ዘሌ. 19፡18

-    አሥርቱ ሕግጋት የብሉይ ኪዳን መሠረቶች ናቸው፡፡ የእግዚአብሔርን ሕግ ብትጠብቁ ብትፈጽሙትም ሕዝቤ ትሆናላችሁ እኔም አምላክ እሆናችኋለሁ ብሎ ቃልኪዳን ገባ፡፡ ሕዝቡም በአንድ አፍ ድምጻቸውን ከፍ አድርገው ‹‹እግዚአብሔር ያለውን ሁሉ እናደርጋለን እንታዘዛለን›› ብለው ቃል ኪዳን ገቡ፡፡ ዘፀ. 19፡8፤ 24፡1-8 ቅዱስ ጳውሎስም እንደነገረን ይህ ፊተኛው ኪዳን ያለ ደም አልተመረቀምና ዕብ. 18፡ 22 ሙሴ ኪዳኑን ለማጽናት የደም መርጨትን ሥርዓት እንዳደረገ በሐዲስ ኪዳንም ቢሆን ሥነ ሥርዐቱ ሙሉ በሙሉ ተቀባይነት ያላቸው ሕግጋት ናቸው፡፡ ማቴ 5፡17፣ 19፡15-22 ፣ዮሐ1፡12 እግዚአብሔር ሕዝቦቹና ልጆቹ ሊያረገን ይህን ታላቅ ተስፋ በመስጠት ቃል ከገባልን እኛ ደግሞ ትዕዛዙን ለመጠበቅ ምን ያህል ቃል ገብተንለታል? ጌታችን ብትወዱኝስ ትዕዛዜን ጠብቁ ዮሐ 14፡15 እንዲሁም ከሆነ እንደ እስራኤላውያን እግዚአብሔር ያለውን ሁሉ እናደርጋለን እንታዘዛለን ብለን ከሁሉ በፊት ለእግዚአብሔር ቃል መግባት አለብን፡፡ ክርስትናውን ስንጀምር የመጀመርያ ሥራችን መሆን ያለበት ይህ ነው፡፡

                   የዐሥርቱ ትዕዛዛት ዓላማ

ዐሥርቱ ትዕዛዛት የተሰጡት በሚከተሉት ዓላማዎች ነው፡፡ ይኸውም፡-

1.  ከግብጽ ምድር ስላወጣቸው ውለታውን እንዲያስቡ
2.  ወደ ፊት በአረማዊያን መካከል ሲመላለሱ ከኃጢአት እንዲቆጠቡ
3.  መንፈሳዊ አካሄዳቸው ምን ምን አቅጣጫ መከተል እንዳለበት ለማሳየት ነው፡፡

የዐሥርቱ ትዕዛዛት አከፋፈል

የክርስቲያን ሕግ የፍቅር ሕግ ነው፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ሌላውን የሚወድ ሕግን ፈጽሞበታል ካለ በኋላ ከዐሥርቱ ትዕዛዛት የተወሰኑትን በመጥቀስ ፍቅር የሕግ  ሁሉ ፍጻሜ መሆኑን በግልጽ ይነግራል፡፡ ሮሜ 13፡8-10 ታዲያ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንዳስተማረ ፍቅር በሁለት ይከፈላል፡፡ ማቴ 22፡34-41

              1 ፍቅረ እግዚአብሔር                                               2 ፍቅረ ቢጽ

1. ፍቅረ እግዚአብሔር ከአንደኛ ትዕዛዝ እስከ ሦስተኛው ያሉት ሲሆኑ እግዚአብሔርን የሚመለከቱ ናቸው፡፡
2ፍቅረ ቢጽ ከአራተኛ ትዕዛዝ እስከ አሥረኛ ትዕዛዝ ያሉት ሲሆኑ በለእንጀራን የሚመለከቱ ናቸው፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ በአዎንታዊና በአሉታ ከመነገራቸው አንጻር በሁለት ይከፈላሉ ይኸውም፡-
      1. ሕግ በአሉታ የተነገሩ /አታድርግ/
      2. ትዕዛዝ በአዎንታ የተነገሩ /አድርግ/

ከዚህም ሌላ ከአፈጻጸማቸው አንጻር ሲታዩ በሦስት ይከፈላሉ፡፡

1.  በሐልዮ የሚፈጸሙ 1፣3፣4 እና 9 በሐሳብ
2.  በነቢብ የሚፈጸሙ 2፣ 8 በመናገር
3.  በገቢር የሚፈጸሙ 5፣6፣7 እና 10 በሥራ ናቸው፡፡

ምንጭ ፡- ሕግጋተ እግዚአብሔር መጽሐፈ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ 3ኛ የተወሰደ እንዲሁም የ/መ/ገ/ጽ/ቅ/ጊ/ቤ/ክ/ሰ/ት/ቤት

ፍልሰታ ለማርያም...


ፍልሰታ ማለት ፈለሰ ከሚለው የግእዝ ቃል የተገኘ ሲሆን ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ ማዛወር የነበሩበትን ሀገር ለቆ ወደ ሌላ ሀገር መሰደድ መፍለስ ማለት ነው፡፡ ጾመ ፍልሰታ ሲባልም የእመቤታችን ሥጋ ከጌቴሰማኒ ወደ ገነት መፍለስን በኋላም በገነት በዕፀ ሕይወት ሥር ከነበረበት መነሣቱን ለማመልከት የሚነገር ነው::