MILLBURN, New Jersey (Reuters) - Floodwaters finally started to recede from areas of the northeast devastated by Hurricane Irene but many communities were still underwater on Wednesday and relief workers battled cut-off roads and raging rivers to deliver emergency supplies.
Wednesday, August 31, 2011
Saturday, August 13, 2011
እንኳን ለጾመ ፍልሰታ በሰለም አደረሳችሁ፤
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን፡፡
ኢትዮጵያ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የአሥራት አገር ናት፡፡ ሊቃውንትም ነቢያት የተነበዩትን ትንቢት የቆጠሩትን ሱባዔ መሠረት በማድረግ ቅድስት ድንግል ማርያም በኪደተ እግሯ ኢትዮጵያን መባረኳን ያስተምራሉ፡፡ «ነቢዩ ዕንባቆምየኢትዮጵያ ድኳኖች ሲጨነቁ ዐየሁ፤» ዕንባ. 3፡7 ብሎ የተናገረው ቃለ ትንቢት እመቤታችን የኢትዮጵያን አውራጃዎች ለመባረኳ ማስረጃ መሆኑን ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ይተረጉማሉ፤ ያመሠጥራሉ፡፡
Thursday, August 4, 2011
እግዚአብሔር፡እረኛዬ፡ነው፥
መዝሙር፡22፡(23)።
የዳዊት፡መዝሙር።
1፤እግዚአብሔር፡እረኛዬ፡ነው፥የሚያሳጣኝም፡የለም።
2፤በለመለመ፡መስክ፡ያሳድረኛል፤በዕረፍት፡ውሃ፡ዘንድ፡ይመራኛል።
3፤ነፍሴን፡መለሳት፥ስለ፡ስሙም፡በጽድቅ፡መንገድ፡መራኝ።
4፤በሞት፡ጥላ፡መካከል፡እንኳ፡ብኼድ፡አንተ፡ከእኔ፡ጋራ፡ነኽና፥ክፉን፡አልፈራም፤በትርኽና፡ምርኵዝኽ፡እነር ሱ፡ያጸናኑኛል።
የዳዊት፡መዝሙር።
1፤እግዚአብሔር፡እረኛዬ፡ነው፥የሚያሳጣኝም፡የለም።
2፤በለመለመ፡መስክ፡ያሳድረኛል፤በዕረፍት፡ውሃ፡ዘንድ፡ይመራኛል።
3፤ነፍሴን፡መለሳት፥ስለ፡ስሙም፡በጽድቅ፡መንገድ፡መራኝ።
4፤በሞት፡ጥላ፡መካከል፡እንኳ፡ብኼድ፡አንተ፡ከእኔ፡ጋራ፡ነኽና፥ክፉን፡አልፈራም፤በትርኽና፡ምርኵዝኽ፡እነር ሱ፡ያጸናኑኛል።
5፤በፊቴ፡ገበታን፡አዘጋጀኽልኝ፡በጠላቶቼ፡ፊት፡ለፊት፡ራሴን፡በዘይት፡ቀባኽ፥ጽዋዬም፡የተረፈ፡ነው።
6፤ቸርነትኽና፡ምሕረትኽ፡በሕይወቴ፡ዘመን፡ዅሉ፡ይከተሉኛል፥በእግዚአብሔርም፡ቤት፡ለዘለዓለም፡እኖራለኹ።
The Lord is my shepherd; I shall not want. He maketh me to lie down in green pastures: he leadeth me beside the still waters. He restoreth my soul: he leadeth me in the paths of righteousness for his name's sake. Yea, though I walk through the valley of the shadow of death, I will fear no evil: for thou art with me; thy rod and thy staff they comfort me. Thou preparest a table before me in the presence of mine enemies: thou anointest my head with oil; my cup runneth over. Surely goodness and mercy shall follow me all the days of my life: and I will dwell in the house of the Lord for ever.
Wednesday, August 3, 2011
የሥነ ልቡና አገልግሎት ለወጣቶች
የሥነ ልቡና አገልግሎት ለወጣቶች
“የአሸናፊነት ምስጢር”
በዶ/ር የማነ ገ/ማርያም
ሰዎች እንደ ተፈጥሮአዊ ጠባያቸውና ዝንባሌአቸው መሠረት በአራት ቦታ ልንመድባቸው እንደምንችል የየሀገሩ የሥነ አእምሮ ወይም የሥነ ልቡና ጠበብት ያረጋግጡልናል፡፡
Tuesday, August 2, 2011
ትምህርተ ጋብቻ
ትምህርተ ጋብቻ ክፍል ፦ ፩
« መጋባት በሁሉ ዘንድ ክቡር ነው፤» ዕብ ፲፫፥፬
ጋብቻን ባርኮና ቀድሶ ለሰው ልጅ የሰጠው እግዚአብሔር ነው። በመሆኑም ጋብቻ የእግዚአብሔር ጸጋ ነው። ስለዚህ በዓይን ምኞት ተጋርደው፥ በሥጋ ፍላጐት ተነድተው ፥ በስሜት ፈረስ ጋልበው ፥ የሚገቡበት ሳይሆን ፦ በጸሎት እና በምልጃ ፈቃደ እግዚአብሔርን ጠይቀው የሚፈጽሙት ታላቅ ምሥጢር ነው።
ቅድስት አርሴማ
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን::
እናታችን ቅድስት አርሴማ እግዚአብሔርን በቅንነት ያገለግሉ ከነበሩ ካህናት ወገን ከሆኑ ከቅዱስ ቴዎድሮስና ከእናቷ ቅድስት አትናሲያ በስዕለት ተወለደች፡፡
ሰማዕቷ ቅድስት አርሴማ ብሉይን ሐዲስን ተምራ እያነበበች እንዲሁም በተግባር እየተረጎመች ዘወትርም በጸሎት ትተጋ እንደነበር ገድሏ ይተርካል፡፡ በዚህ ዘመን ድርጣድስ የሚባል በአርመን የነገሠ አረማዊ ንጉሥ ለጣዖት የሚሰግድ' ፀሐይንም የሚያመልክ' ክርስቲያኖችንም እኔ ለማመልከው አምላክ መስገድ አለባችሁ በማለት መከራ ያጸናባቸው ነበር፡፡
Subscribe to:
Posts (Atom)